ኣማርኛ (amarəñña)

IBA Montage

በዓለም ቀዳሚ የንግድ ስራ ሽልማት ፕሮግራም ለሆነውለ2025(22ኛውዓመታዊ )ዓለም አቀፍ የንግድ ስራ ሽልማት (International Business Awards®) ድርጅትዎ ዕጩዎችን እንዲያቀርብ እንጋብዛለን።

የእጩነት ጥያቄዎን እንዴት አዘጋጅተው ማቅረብ እንዳለብዎት የተሟሉ መመሪያዎችን የያዘ የመግቢያ ኪት ለማግኘት ከፈለጉ፣ የኢሜይል አድራሻዎን እዚህ ይጻፉትና በኢሜይል እንልክልዎታለን። በጣም ጥብቅ የሆነ የግላዊ መረጃ ፖሊሲ ስላለን በማንኛውም ምክንያት ቢሆን የኢሜይል አድራሻዎን ለሌላ ሰው አናጋራም።

 



በዚህ ድረ ገጽ ላይ በዚህ ቋንቋ የተጻፈ ብቸኛው ገጽ ይህ ነው። ሌሎቹ ገጾች በሙሉ ግን ልክ እንደመግቢያ ኪቱ ሁሉ በእንግሊዝኛ የተጻፉ ናቸው። የዚህ ምክንያት ደግሞ በዓለም ላይ ያሉ የቢዝነስ ባለሙያዎች በዳኝነት ሒደቱ ለመሳተፍ እንዲያስችላቸው ሲባል የእጩነት ማመልከቻዎች በእንግሊዝኛ እንዲቀርቡ ስለምንጠይቅ ነው።

International Business Awards በተመለከተ

International Business Awards በእያንዳንዱ የስራ ቦታ ዘርፍ ለተመዘገቡ ስኬቶች ዕውቅና የሚሰጥ ብቸኛው ዓለም አቀፍ የሽልማት ፕሮግራም ነው። ሽልማቶቹን የሚያቀርበው የ Stevie Awards ድርጅት ተቀማጭነቱ በዩናይትድ ስቴትስ ነው። ሰባት የተለያዩ የ Stevie Awards ውድድሮችን የምናዘጋጅ ሲሆን ይህን በተመለከተ መረጃ ከዚሀ ድረ ገጽ ማግኘት ይችላሉ፡ www.StevieAwards.com። የ Stevie Award ዋንጫ በዓለም ላይ ለማግኘት ከሚመኟቸው ሽልማቶች መካከል አንዱ ነው።

በ2024 ዓለም አቀፍ የስቲቭ ሽልማት (International Stevie Awards) ከ60 በላይ ሃገራት ለመጡ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሽልማቱ ተሰጥቷል። የ2024 ተሸላሚዎችን ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።​

 

ምድቦች

በ International Business Awards ውስጥ በርካታ ዓይነት የሽልማት ምድቦችን መምረጥ ይችላሉ። ለመሳተፍ ከወሰኑ፣ ድርጅትዎ ዕውቅና ሊያገኝባቸው የሚፈልግባቸው ስኬቶች ጋር የሚዛመዱትን ምድቦች መርጠው በእነዚያ ምድቦች መመሪያዎች መሰረትም እጩነትዎን ያዘጋጃሉ። ዝግጁ ከሆኑ የሽልማት ምድቦች የሚከተሉት ናቸው፡

• የዓመቱ ስኬታማ ድርጅት ሽልማት (Company of the Year Awards)
• የሕዝብ ግንኙነት ሽልማት (Public Relations Awards)
• የደንበኞች አገልግሎት ሽልማት (Customer Service Awards)
• የሰው ሐብት ሽልማት (Human Resources Awards)
• የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሽልማት (Information Technology Awards)
• የስራ አመራር ሽልማት (Management Awards)
• የማርኬቲንግ ሽልማት (Marketing Awards)
• ሁሉም ዓይነት ሚድያ፣ ማለትም የድረ ገጽ ሽልማት፣ የዓመታዊ ሪፖርት ሽልማት፣ የኢቨንት ሽልማትና የቪድዮ ሽልማት (Web Awards, Annual Report Awards, Event Awards, and Video Awards)
• የንግድ ስራ አፈጻጸም ሽልማት (Business Performance Awards)
• የአዳዲስ ምርቶች ሽልማት(New Product Awards)

የምድቦቹ ዝርዝርና መግለጫ፣ የእያንዳንዱ የማቅረቢያ መስፈርቶች፣ የማስገቢያ ቀነ ገደብና ማንኛውም የመግቢያ ክፍያ በመግቢያ ኪት ውስጥ ተዘርዝሯል።

በአብዛኞቹ ምድቦች እርስዎ ወይም ድርጅትዎ በተመረጠው ምድብ ስላስመዘገባችሁት ስኬት የሚያሳይ ከአምስት (5) ደቂቃ ያልበለጠ ቪዲዮ ወይም በምድቡ ለተዘጋጁ ጥያቄዎች የጽሁፍ መልስ የማቅረብ አማራጭ አለዎት።

 

ሽልማቶች

በ2025 ዓለም አቀፍ የስቲቭ ሽልማት (International Stevie Awards) ኦገስት 13 ቀን ይፋ ይደረጋል። ከዚያ ቀጥሎ የStevie Award ዋንጫዎች፤ እና የብር እና የነሃስ ሜዳሊያዎች በኦክቶበር ወር በአውሮፓ ውስጥ በሚካሄድ ስነ-ስርዓት ይሰጣሉ።

 

አድራሻ

እባክዎ የ International Business Awards ወይም የ Stevie Awards በተመለከተ ያለዎትን ማንኛውም ጥያቄ ያሳውቁን።

The Stevie Awards
10560 Main Street, Suite 519
Fairfax, Virginia 22030, USA
ስልክ፡ +1 703-547-8389
ፋክስ፡ +1 703-991-2397
ኢሜይል፡ help@stevieawards.com